ዕጩ የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ
የሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ ባለአክስዮኖች ባካሄዱት 26ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር SIB/48/2019 መሠረት የቦርድ አባላት አስመራጭ ኮሚቴ መመረጡ ይታወቃል፡፡
በዚሁ መሠረት ኮሚቴው ዕጩ የዲሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ከሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ መስከረም 18 ቀን 2014 ዓ. العاب مقابل المال ም ብቻ ስለሚቀበል በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች በተለይም ቁጥር SIB/48/2019 እና SIB/32/2012 ላይ የተዘረዘሩትንና በሚከተለው ሁኔታ የቀረቡትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እጩዎችን እንድትጠቁሙ ለመላው የኩባንያችን ባለአክስዮኖች ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
- የሕብረት ኢንሹራንስ ባለአክስዮን የሆነና የቦርድ አባል ሆኖ ለመስራት ፈቀደኛ የሆነ፣
- ዕድሜው 30 አመትና ከዚያ በላይ የሆነ፣
- በንግድ ሥራ አመራር የሥራ ልምድ ያለው፣ በተለይም በኢንሹራንስ ሥራ ልምድ ያለው ቢሆን ተመራጭ ይሆናል፡፡
- በማንኛውም ኢንሹራንስ ኩባንያ ሠራተኛ ያልሆነ፣
- ሀቀኛ፣ ታማኝና መልካም ዝና ያለው፣ በተለይም በማጭበርበር፣ እምነት በማጉደል፣ ትክክለኛ ያልሆነ የሂሳብ መግለጫ በማቅረብና በመሳሰሉት ተከሶ በፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶበት የማያውቅ፣
- በሌላ የፋይናንስ ድርጅት ውስጥ የቦርድ አባል ያልሆነ፣
- በራሱ ወይም በሚመራው ወይም ዳይሬክተር በሆነበት ድርጅት ላይ የመክሰር ክስ ያልቀረበበት ወይም የኪሳራ ውሳኔ ያልተሰጠበት፣
- በኪሳራ ምክንያት ንብረቱ የእዳ ማቻቻያ ሆኖ ያልተወሰደበት፣
- የባንክ ብድር ባለመክፈሉ ምክንያት ንብረቱ በሐራጅ ያልተሸጠ፣ ተከሶ ያልተፈረደበት ወይም እሱ የሚመራው ወይም ዳይሬክተር የሆነበት ድርጅት ከገንዘብ ተቋማት የተበደረውን ገንዘብ ባለመክፈሉ ብድሩ ጤናማ ወዳልሆነ የብድር ሁኔታ ያልገባበት (NPL ያልሆነበት)፣
- ከሚመረጡት የቦርድ አባላት 75% የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ከዚያ በላይ ሊኖራቸው የሚገባ ሲሆን የተቀሩት 25% ቢያንስ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቁ መሆን አለባቸው፡፡
- በቂ ስንቅ/ገንዘብ ሳይኖረው ቼክ ሰጥቶ ሂሳቡ ያልተዘጋበት፣
- ታክስ ባለመክፈል ተከሶ ጥፋተኛ ያልተባለ፣
- የቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ አባል ያልሆነ እና፣
- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች ላይ የተገለጹ ሌሎች መመዘኛዎችን የሚያሟላ፡፡
በመሆኑም ጥቆማውን “ዕጩ የቦርድ አባላትን ለመጠቆም የተዘጋጀ ቅጽ” በሚል የተዘጋጀውን ፎርም በመሙላት
*ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ. (ኩባንያ) ዋና መስሪያ ቤት 10ኛ ፎቅ የዋና ሥራ አስኪያጅ ፀሐፊ ቢሮ በተዘጋጀው መዝገብ ላይ በአካል ቀርቦ በማስመዝገብ መስጠት ፣ ወይም
* በመልዕክት ሳጥን ቁጥር 1156 ለሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ የዲሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ ጽ/ቤት በማለት መላክ ፣ ወይም
* በኢ-ሜይል አድራሻችን nominationc@unic-ethiopia.com መላክ ይቻላል፡፡
ማሳሰቢያ
- የጥቆማ ማቅረቢያውን ቅጽ
- ከሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ. ዋና ሥራ አስኪያጅ ፀሐፊ ቢሮ ወይም በኩባንያው ቅርንጫፍ መ/ቤቶች ወይም ከኩባንያው ድረ ገጽ www.unic-ethiopia.com ማግኘት ይቻላል፡፡
በተጨማሪም ቅጹ ባለአክስዮኖች በአክስዮን ግዢ ጊዜ ባስመዘገቡት የፖስታ አድራሻ ይላካል፡፡
- ከመስከረም 18 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት በኋላ የሚቀርቡም ሆነ ከዚህ በኃላ በፖስታ ወይም በኢ-ሜይል የሚደርሱ ጥቆማዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
- የሕግ ሰውነት ያለው ባለአክስዮን ጥቆማ ሲያደርግ በጥቆማ ማቅረቢያ ቅጹ ላይ የተገለፁትን ማሳሰቢያዎች ተግባራዊ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
- በተባዕት ጾታ የተገለፀው በሙሉ ለአነስታይ ጾታም ያገለግላል፡፡
- ከሚጠቆሙት ዕጩዎች መካከል 1/3ኛ የሚጠቆሙት ከኩባንያው ጠቅላላ የተፈረመ አክስዮን ውስጥ ከ2% በላይ በያዙ ባለአክስዮኖች ነው፡፡ የተቀሩት 2/3ኛ ዕጩዎች ደግሞ በሁሉም ባለአክስዮኖች የሚጠቆሙ ናቸው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያና አስተያየት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፀሐፊ ቢሮ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0114671874 መደወል ይቻላል፡፡
የዲሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ
ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ.